onsdag 23. oktober 2013

አብረን እንነሳ (ከማንደፍሮ መንግስቱ በርገን ኖርዌይ)

እውነት በተነወረበት ሀቅ በተገደፈበት ምድር

ሸፍጥ በነገሰበት ሀሰት በተሞሸረበት ሃገር

የህዝብ ጆሮ ሲራብ እውነታን ማወቅ ሲጠማ

ስውሩን ሲገለጥለት ክስተቱን እናደለ ሲሰማ

መብቱ ሳይደፍሩ ፍቃዱን ሳይከለክሉ

ሰብናውን ሳያሳንሱ ነፃነቱን ሳያጎሉ

እነሆ አውነታውን ስማና እውቀውና ፍረደን ቢሉ

በህዝብ ልብ ይከብራሉ በህዝብ አይን ይጎላሉ

እንጂማ መብቱን ቢሸራርፉ

ፈቃዱን ቢያጎድፉ

በፍላጎቱ ቢያሾፉ

አልጋው ተመቸ ብለው ቢቀብጡ

በኔ ይሁንቦ አይቀሬ ነው ወድቆ ለመላላጡ

ግና ዘመን እስኪመጣ

ብሩህ ቀን እስኪወጣ

እነሆ ሀቅ ላትደበቅ እውነት ወግጅ ላይሉ

ልክ እንደቀድሞ የውሸት ግዳይ ላይጥሉ

የተነገረው እንደተነገረው የተፈጠረው እንደተፈጠረው … የሀቅ ግነት የለውም እንዲሉ

የህዝብን እንባ የትውልድን መከራ

ጭቆናና መድሎ እንዲሁም የዘረኝነት ሴራ

አደባባይ የሚያወጣ ከወገናዊነት የጠራ

ለኢትዮጵያዊነት የሚሰራ

ኢሳት ተወልዶ የወገንን እንባ ሲያብስ ማየቱ

ሀቅን እየገለጠ የሀገርን ምጽንታ መስማቱ

ለምጡዋ ምላሽ ለእንባዋ ማበሻ ልጆቹዋ ሲበረቱ

ወገን ካለበት ተጠራርቶ አንድነቱን ሲያሳይ

በሃብቱ በገንዘቡ በእውቀቱ የድርሻወን ሲያረግ ያለከልካይ

ኢሳት እሳት ሆኖ ገለባውን ሲበላ

ሀሰት አመድ ሆኖ እውነት እንደ ወጋጋን ሲያቅላላ

ትግሉ ነዶ ግሞ

እንደ ገሞራ ግሞ

የነዲዱ ወገግታ ካድማስ ሞዶ ይታየኛል

የፀዳሉ ግርማ የትንታጉ ጩኸት ይሰማኛል

እናም ወገኔ ሃገር ረዳት በምትሻበት በእንዲህ አይነቱ ሰአት

የሰው ያለ እያለች በምትጣራበት ወራት

ወገኔ ሆይ ጆሮህንም ኪስህንም አትንፈጋት

ይልቁንስም ለንዲህ አይነቱ ጥሪ ለመከራ ጩኸቱዋ

ሁንላት አይዞሽ ባይ ሁንላት ረዴቱዋ

ለእውንት ለሚታገል ለህዝብ ድምጽ ከሚሰራ

ከጭቁኖች ልሳን ታገል ከኢሳት ጋራ

አንድ ላይ ተንስ ጨለማው ላይ አብራ፡
                                                                                                 

                                                    ኢትዮዽያ ለዘላለም ትኑር

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar